ሐሃይለማርያም ደሳለኝና ቴድሮስ አድሀኖም የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያስገድደውን አዲሱ ስምምነት ከሀገራት ቀድመው መፈረማቸው ታውቋል።

source freedom4ethiopian

የጥገኝነት ጥያቄያቸውሐሃይለማርያም ደሳለኝና ቴድሮስ አድሀኖም የሚባሉ የወያኔ ተላላኪዎች በአሁኑ ወቅት ቤልጅየም ብራሰልስ የሚገኙ ሲሆን በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት ስደተኞችን በሀገራቸው ለመገደብና ተቀባይነት ያላገኙትን ወደ መጡበት ለመመለስ ለሚያስችለው ስምምነት ከ62ቢሊዮን ዩሮ በላይ በጀት መመደቡን ተከትሎ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞችን ወደ እናት ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያስገድደውን አዲሱ ስምምነት ከሀገራት ቀድመው መፈረማቸው ታውቋል።

እነዚህ ጨቋኝ የዜጎችን ደም የሚጠጡ አምባገነኖች እንደዚህ አይነቱን በሰበብ አስባቡ ከፈረንጅ የሚወረወርላቸውን ዳርጎት ለአገዛዙ እኩይ ምግባርና የጭቆና ቀምበር ለመጠቀም ከሀገራት ሁሉ ተሽቀዳድመው ፈራሚ መሆናቸው ታውቋል።

ስምምነቱን ሀይለማርያም ደሳለኝና የአውሮፓ ህብረት ኮምሽነር ጃን ክላውድ ጃንከር ማክሰኞ ዕለት በብራስልስ ተፈራርመዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የአውሮፓ ህብረት ከተለያዩ የአፍሪቃ አፋኝ መንግስታት ጋር የተናጠል ስምምነት በማድረግ ስደተኞችን ላለመቀበል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በርካታ የስብዓዊ መብት ድርጅቶች እያወገዙት ይገኛሉ።

ስምምነቱ ከዚህ ቀደም የአውሮፓ ህብረት ከአፍሪቃ አህጉር ጋር በጋር ችግሮች ዙሪያ ለመስራት ያደረገው ስምምነት አካል መሆኑም ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <strike> <strong>

Visit Us On FacebookVisit Us On Youtube